petroleum fuel

ተፅዕኖው የገዘፈው የነዳጅ ዋጋ ማሻሻያ

የኢትዮጵያ ምጣኔ ሀብት ከዓለም አቀፉ የገበያ ሥርዓት ተነጥሎ በራሱ እንዳይቆም ከሚያስገድዱት አንዱ ነዳጅ ነው፡፡ በማዳበሪያ፣ ድንጋይ ከሰልና ብረት በቅርቡ ራሳችንን እንችላለን ብለው የተነሱት የማዕድን ሚኒስትሩ እንኳን ኢትዮጵያ በነዳጅ ራሷን ትችላለች ለማለት አልደፈሩም፡፡